ባንካችን “አቢሲንያ- ቪዛ 2026 የፊፋ ዓለም ዋንጫ” በሚል መጠሪያ ከቪዛ ጋር በጋራ ባካሄደው የሽያጭ ዘመቻ ላይ የዓለም ዋንጫን ለመታደም ዕጣ ለወጣላቸዉ አራት ዕድለኞች የሽኝት መርሐ-ግብር አካሄደ።
ትናንት ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ.ም በባንካችን ዋና መ/ቤት በተካሄደው የሽኝት መርሐ-ግብር ላይ የባንካችን ቺፍ ዲጂታል ባንኪንግ ኦፊሰር ወ/ሮ ሶስና መንገሻ እንደተናገሩት እነዚህ ዕድለኞች አስፈላጊውን የጉዞ ፈቃድ ያገኙና የ2026 የፊፋ የዓለም ዋንጫ አዘጋጅ ከሆኑት 3 ሃገራት ማለትም አሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ መካከል ወደ አሜሪካ የሚጓዙ ናቸው ብለዋል።
እነዚህ ዕድለኛ የሆኑ የባንካችን ደንበኞች አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ ያሟሉና ለጉዞ የሚያስፈልጋቸውን ቪዛ ያገኙ ሲሆን የደርሶ መልስ የጉዞ ትኬት፣ የአራት ቀናት የሆቴል ቆይታ እና ውድድሩን መከታተያ የስታዲየም መግቢያ ትኬት የተመቻቸላቸው መሆኑን በመድረኩ ላይ ተገልጿል።
በዚህ ከማርች 9 እስከ ኤፕሪል 15 ቀን 2026 ድረስ በተካሄደ የሽያጭ ዘመቻ የባንካችንን ቪዛ ካርድ ተጠቅመው በፖስ ማሽኖቻችን ላይ ከብር 1,000 ጀምሮ ግብይት ያከናወኑ ደንበኞች በሽልማት ዕጣው እንደተካተቱም ቺፍ ኦፊሰሯ ጠቁመዋል።
በመጨረሻም ወ/ሮ ሶስና ለተጓዦቹ በሚሄዱበት አሜሪካ ጥሩ ጊዜ እንዲያሳልፉ መልካም ምኞታቸውን ገልጸው፣ በሚኖራቸው ቆይታም ባንካችንን እና ሃገራችንን በበጎ እንዲያስተዋውቁ አደራ ብለዋል።
በሽኝት መርሐ-ግብሩ ላይ የባንካችን የበላይ ሥራ አመራር አባላት፣ የባንካችን አጋር የሆነው የቪዛ ኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ተወካዮች፣ የሚዲያ ባለሙያዎች እና ታዋቂ የስፖርት ተንታኞች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ ተደረገላችሁ እንግዶች ተገኝተዋል።
በቅርቡም ባንካችን በነበሩት የ”ይጀምሩ_ያድሱ_ይደጉ” እና የ”እችላለሁ!” የሽያጭ ዘመቻዎች ሁለት ዕድለኛ ደንበኞቹን ሃዩንዳይ አክሰንት ሴዳን እና የ2025 ቢ.ዋይ.ዲ ሴጉል መኪና እንደሸለመ የሚታወስ ነው።










