የአቢሲንያ ባንክ የባለአክሲዮኖች 24ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ኅዳር 10 ቀን 2013 ዓ.ም. በኢንተርኮንትኔንታል አዲሰ ሆቴል ተካሂዷል፡፡የጠቅላላ ጉባዔው በተመደበላቸው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ከመጀመራቸው በፊት የተለያዩ መርሐ-ግብሮች ቀርበዋል፡፡ከእነዚህም መካከል በዘጋቢ ፊልም የቀረበ የባንኩ የ25 ዓመታት ጉዞ ሲሆን መስራች የአክሲዮን ባለቤቶች፣ ድርጅቱን በቦርድ አባልነት ያገለገሉ፣ በባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ያገለገሉ እንደሁም አሁንም በማገልገል የሚገኙ፣ ነባር የድርጅቱ ሠራተኞች...