ባንካችን በቅርቡ ያስተዋወቀውን የPayment Gateway Technology በመጠቀም በተለያዩ የዓለም ሀገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የእጅ ስልካቸውን ብቻ በመጠቀም ለወዳጅ ዘመዶቻቸው በቀላሉ ገንዘብ መላክ የሚችሉበት መንገድን ፈጥሯል፡፡ ከዚህም ባሻገር የሕዝብና የመንግስት ፕሮጀክቶችን ለመደገፍ በሚዘጋጁ የተለያዩ የድጋፍ ማሰባሰብያ ፕሮግራሞች ላይ በውጭ ሀገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በቀላሉ ለሀገራቸውም ሆነ ለወገናቸው መድረስ የሚችሉበት ሁኔታ በአቢስንያ ባንክ...
Category:
አቢሲንያ በአውታር የጥበብ ገበታ!
አቢሲንያ ባንክ የሀገራችን የሙዚቃ ጥበብ እንዲያድግ ካለው ፅኑ ፍላጎት የተነሳ የኢትዮጵያ ሙዚቃ በየትኛውም የዓለማችን ጫፍ ባሉ የሙዚቃ አፍቃሪዎች ዘንድ ተደራሽ መሆን የሚችልበትን የክፍያ ቴክኖሎጂ ዘርግቷል፡፡ከእንግዲህ ወዲያ የሀገራችን ሙዚቀኞች ሥራቸውን ለዓለም ገበያ አውታር በተሰኘው የሙዚቃ መተግበሪያ በኩል ለሽያጭ ሲያቀርቡ አቢሲንያ ባንክ የክፍያውን መንገድ በማመቻቸት ከጎናችሁ ነን ይላል፡፡ በየትኛውም የዓለማችን ጫፍ ያለ የሙዚቃ አፍቃሪ የቪዛ እና ማስተር...
ወለድ አልባ የብድር ጥያቄ በባንኮች እንዴት ይስተናገዳል?
የሀገራችን ባንኮች ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት መስጠት ከጀመሩ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በቅርቡም ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት የሚሰጡ ባንኮች እንዲቋቋሙ በመንግሥት የተሰጠውን የማበረታቻ ውሣኔ ተከትሎ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ማውጣቱ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም በአሁኑ ወቅት ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነጻ የሆነ የባንክ አገልጋሎት ለመስጠት ያቀዱ አክሲዮን ማኅበራት በምሥረታ ላይ ይገኛሉ ፡፡ ይህም በሀገራችን ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት...
ምንም እንኳን ሀገራችን ኢትዮጵያ ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ብትመደብም ህዝቦቿ የራሳቸውን ኑሮ ለማሻሻል በሚያገኟቸው አነስተኛ ገቢ የተለያዩ አማራጮችን ሲጠቀሙ ይታያል፡፡ ከዚህም ውስጥ አንዱ ዕቁብ ሲሆን፣ በማኅበረሰባችንም ውስጥ ትልቁን ድርሻ ይወስዳል፡፡የአቢሲንያ የዕቁብ የቁጠባ ሂሳብ በሚይዙዋቸው የአባላት ብዛት እና በሚሰበስቧቸው የገንዘብ መጠን ከፍተኛ፣ መካከለኛ እንዲሁም አነስተኛ በመባል የተመደቡ ሲሆን እንደ መጠናቸው የየራሳቸው መለያዎች እና የሚያስገኛቸው ጥቅሞች እንደሚከተሉት...
ባንካችን በጅማ ንግድ ትርኢትና ባዛር ላይ በአንደኛ ደረጃ አጋርነት ተሳተፈ!
አቢሲንያ ባንክ በጅማ ከተማ ከጥር 03 እስከ 24/2013 በቆየው 10ኛዉ የጅማ ንግድ ትርኢትና ባዛር ላይ በአንደኛ ደረጃ አጋርነት ተሳታፊ ሆኗል፡፡ በባዛሩ ላይ ባንኩ የማህረሰቡ እና የከተማው የልማት አጋር መሆኑን በማሳየት ለዝግጅቱ ድምቀት ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል፡፡ አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!
ባንካችን አቢሲንያ ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው ጀግኖች ውስጥ የመጀመሪያ ረድፍ ላይ በሚቀመጡትና ስማቸውን በታሪክ በወርቅ ቀለም ባጻፋት በብ/ጄነራል ለገሰ ተፈራ ስም ቅርንጫፍ ከፈተ፡፡
አሁንም ባንካችን የሀገር ባለውለታዋችን በስማቸው ቅርንጫፎችን በመሰየም እየዘከራቸው ይገኛል፡፡ ይህም ለሀገራችን ዘመን አይሽሬ አበርክቶ ያደረጉ ባለውለታዎች ስማቸውን እና መልካም ተግባራቸውን ለመዘከር እና ለቀጣዩ ትውልድ ለማሳወቅ እና ትምህርት እንዲሆን በማሰብ ነው፡፡ጥቂት_ስለ_ብ_ጄነራል_ለገሠ_ተፈራ የሱማሊያ መንግስት ኢትዮጵያን ወረረ፡፡ በወቅቱ የሱማሊያ ፕሬዝደንት ዚያድባሪ ኢትዮጵያን የወረረው፣ የደርግ መንግሥት በጦርነት በተጠመደበት ወቅት ነበረ፡፡ የተረጋጋ መንግሥት እያላት ኢትዮጵያን መውረር አጸፋው ከባድ እንደሆነ የተረዱት...
የባንኮች ብድር አሰጣጥና ለመበደር የተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎች
የብድር አሰጣጥ ሂደቶች ከባንክ ባንክ የተለያዩ እንደመሆናቸው የብድር መመሪያዎችና ፖለሲዎችም እንዲሁ ከተቋም ተቋም በተወሰነ ደረጃ የተለያዩ ናቸው፡፡ ነገር ግን ባንኮች የብድር ማመልከቻ ከመቀበል ጀምሮ ደንበኛ ወይም ተበዳሪ የሚፈልገውን የብድር መጠን ለመፍቀድ እንዲሟላ የሚፈልጉት፣ የጋራ መሠረታዊ ቅድመ ሁኔታዎች እንዲሁም መስፈርቶች አሉ፡፡ አነዚህን መስፈርቶችና ጉዳዮች በሚገባ መገንዘብና አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ በሂደት ማሟላት የብድር ጥያቄ ውድቅ እንዳይሆን ከማገዝ...
የገንዘብ ምንዛሬ ፋይዳውና ተፅዕኖው
ገንዘብ ምንድን ነው? ቀደም ባሉት ጊዜያት እንደሚታወቀው ሰዎች ግብይታቸው ቁስን በመለዋወጥ ወይም ዕቃን በዕቃ በቀጥታ መለዋወጥን መሰረት ያደረግ የንግድ እንቅስቃሴ ነበረ፡፡ ይህ ማለት አንድ ሠው ዕቃ ለመሸመት ከፈለገ፤ ያን የፈለገውን ዕቃ የሚያቀርብለትን አካል ወይም ግለሰብ ፍላጎት ሊያሟላ የሚችል ተለዋጭ ዕቃ ይዞ መገኘት እና መቅረብ የግድ ይለው ነበር፡፡ ይህ በምጣኔ ኃብት አነጋገር – የጥምር ፍላጎት ግጥምጥሞሽ...
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረስዎ!
ለበዓሉ ማድመቂያ ከውጭ ከወዳጅ ዘመድዎ የሚላክልዎትን ገንዘብ በባንካችን ሲቀበሉ! በእጅዎ ያለ የውጭ ሀገር ገንዘብ ካለዎትም በባንካችን ሲመነዝሩ!በሀገራችን የመጀመሪያ በሆነው E-Commerce አገልግሎታችን፤ ዓለም አቀፍ ካርዶችን በመጠቀም ክፍያዎችን ሲፈፅሙ! እኛ ደግሞ በ3ኛውዙር የእንሸልምዎ መርሐ ግብር ዕድለኞችን ለመሸለም ተሰናድተናል፡፡እደጅዎ ባሉ ከ570 በላይ በደረሱ ቅርንጫፎቻችን በኩል ይቀበሉ ራስዎንም ለሽልማት ዕጩ ያድርጉ!
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውንና ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) መሠረት ንብረቶቹ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋውን ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው ለመሳተፍ ይችላሉ፡፡...








