እንደሚታወቀው አቢሲንያ ባንክ እ.ኤ.አ ከ2017 ጀምሮ ዘመናዊ ኮር ሲስተምን (R17 Temenos T-24 Islamic Module) በመጠቀም ለደንበኞቹ የተለያዩ ከወለድ ነፃ አገልግሎቶችን ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ አሁን ደግሞ እጅግ በጣም ዘመናዊ የሆነ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ውድ ደንበኞቹ ማራኪ የሆኑ ፕሮዳክቶችንና አገልግሎቶችን ለመስጠት የትግበራ ስራ ጀምሯል፡፡
በመሆኑም ዓለም አቀፍ የኢዝላሚክ ባንኮችና ተቋማት ሶሉሽንስ እና አገልግሎቶች አቅራቢ ከሆነው ፓዝ ሶሉሽንስ
(Path Solutions) ከተባለው ታዋቂ ተቋም ጋር በጋራ በመሆን ሁሉን አቀፍ የሆነ የትርፍ ማስያና ማከፋፈያ ሲስተምን ለመዘርጋት የተለያዩ ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡
ይህ በትግበራ ላይ ያለ እጅግ ዘመናዊ የሆነ ስርዓት (iMAL*PCS) በአጠቃላይ ከወለድ ነፃ የሆኑ ፕሮዳክቶችን ትርፍ ለማስላትና ለማከፋፈል ጉልህ ጠቀሜታ ያለው ስርዓት ነው፡፡
በተጨማሪም ይህ ስርዓት በሸሪያ መርሆዎች ላይ ተመርኩዞ የደንበኞችን ፍላጎት የሚያሳድግና ሁሉንም ትርፎች አነዚህን መርሆች በመከተል በፍጥነት ለማከናወን የሚያግዝነው፡፡ በተጨማሪም ትርፍን ለማከፋፈል የሚረዱ መርሆዎችንም ለማስቀመጥ የሚረዳ ነው፡፡
በአጭሩ ይህ በባንኩ ውስጥ በትግበራ ላይ የሚገኝ አዲስ ኢዝላሚክ ኮር ባንኪንግን (Islamic Core Banking) በአዲሱ የኢዝላሚክ ኮር ባንኪንግ ሲስተም (Islamic Core Banking system) ሙሉ በሙሉ የሚተካ ነው፡፡
ይህን ዘመናዊ ስርዓት በተመለከተ በባንኩ ከወለድ ነፃ ባንክ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን “ከኢዝላሚክ ባንኪንግ ጋር የሚሄዱ የተለያዩ ሶፍትዌሮችን በሚገባ ስናጤን ቆይተን አሁን ይህን የፓዝ ሶሉሽንስ ፕሮዳክት የሆነውን ዘመናዊ ሶፍትዌር (iMAL) የመረጥንበት ምክንያት ሶፍትዌሩ ካለው ሰፊና ሁሉን አቀፍ ባህሪያት እንዲሁም ከኤ.ኤ.ኦ.አይ.ኤፍአይ. የሸሪያና አካውንቲንግ መለኪያዎች (AAOIFI’s Sharia and accounting standards)ጋር ተስማሚና አብሮ የሚሄድ በመሆኑ ነው” ብለዋል፡፡
ዳይሬክተሩ አክለውም “ከፓዝ ሶሉሽንስ ጋር የሚኖረን ጥምረት በሃገራችን ውስጥ በኢዝላሚክ ፋይናንስ ዘርፍ የደንበኞችን ፍላጎት በሚገባ በማርካት ተወዳዳሪ ሆኖ ለመውጣት እጅግ በጣም የሚያግዝ ነው” ሲሉ ገልፀዋል፡፡
አቶ አብዱልቃድር ጨምረውም “ይህ አዲስ ስርዓት በሸሪያ መርሆዎች መሰረት የተጣራ ገቢን ለማስላትና ለማከፋፈል ትልቅ ጠቀሜታ ያለው ሲሆን በተጨማሪም ከሸሪያ መርሆዎችጋር የሚሄዱ ለየት ያሉና አዳዲስ ፕሮዳክቶችን ለደንበኞች ለማቅረብ የማይተካ ሚና ይኖረዋል” ብለዋል፡፡
Leave a Reply