ባንካችንና ቪዛ የዓለም ዋንጫን ለመታደም ዕጣ የወጣላቸውን የ5ኛ እና የመጨረሻው ዙር ዕድለኞች ይፋ አደረጉ

ባንካችንና ቪዛ የዓለም ዋንጫን ለመታደም ዕጣ የወጣላቸውን የ5ኛ እና የመጨረሻው ዙር ዕድለኞች ይፋ አደረጉ

• ዕድለኞቹ ለአሜሪካው የዓለም ዋንጫ ጉዞ እየተዘጋጁ ነው

ባንካችን አቢሲንያ እና ቪዛ ደንበኞችን ለማበረታታት ብሎም ለመሸለም የ2026 ፊፋ ዓለም ዋንጫን በስፍራው በአካል ተገኝተው ለመከታተል የሚያስችል ዕጣ የወጣላቸውን የአምስተኛ እና የመጨረሻ ዙር 4 ዕድለኞች በጋራ ይፋ አደረጉ። 

ትናንት ሚያዚያ 6  ቀን 2018 ዓ.ም በዋናው መ/ቤት የባንካችን የሥራ ሐላፊዎችና የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ታዛቢዎች በተገኙበት መርሐ ግብር ላይ የባንካችን የዲጂታል ከስተመር አኪዩዜሽን ዳይሬክተር አቶ አባይ ስሜ የዕጣ ማውጣቱን ሥነ-ሥርዓት በይፋ አስጀምረዋል።

በወጣው ዕጣ መሠረትም 2 የማዕከላዊ አዲስ ዲስትሪክት ደንበኞች (የዕጣ ቁጥር  600036806  እና 700052890) ፣1 የምስራቅ አዲስ ዲስትሪክት ደንበኛ (የዕጣ ቁጥር 500029730) እና 1 የሃዋሳ ዲስትሪክት ደንበኛ (የዕጣ ቁጥር 700047357) በድምሩ 4 የባንካችን ደንበኞች ዕድለኞች ሆነዋል። 

በዚህ የሽያጭ ዘመቻ ጠንካራ የደንበኞች ተሳትፎ የታየ ሲሆን፣ ባለፈው አንድ ሳምንት ብቻ ከ 15,000 በላይ ኩፖኖች የአቢሲንያ ባንክ ቪዛ ካርዶችን በመጠቀም ከ1,000 ብር በላይ ግብይቶችን ለፈጸሙ ደንበኞች ተልከዋል። 

ይህ የሽያጭ ዘመቻ በባንካችን እና በቪዛ መካከል በመላው ኢትዮጵያ የክፍያ ስርዓቶችን ፍጥነት፣ ደህንነት እና ቅልጥፍና ለማሻሻል ያለመ ሰፊ ስትራቴጂካዊ ትብብር አካል ነው። 

በአጠቃላይ በነበሩ 5 ዙሮች 20 ደንበኞች የዚህ የሽያጭ ዘመቻ ዕድለኞች የሆኑ ሲሆን የእስካሁኖቹ ዕድለኞች የ2026 የፊፋ ዓለም ዋንጫን በአካል ለመታደም የጉዞ ዝግጅት እያደረጉ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button