ባንካችን አቢሲንያ ከ232 በላይ ሽልማቶችን ለባለዕድለኞች አስረከበ!

ባንካችን አቢሲንያ ከ232 በላይ ሽልማቶችን ለባለዕድለኞች አስረከበ!

2 የ2020 ኒሳን የቤት መኪኖችን ጨምሮ በአጠቃላይ 232 ሽልማቶችን ለባለ ዕድለኞች ያሸልም የነበረው “መቆጠብ ያሸልማል” እና የ“እንሸልምዎ” መርሐ-ግብሮች ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. አዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም ዲስትሪክቶች የሽልማት አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓቱ በድምቀት ተካሄደ!
በአዲስ አበባ በሂልተን ሆቴል በተካሄደው የሽልማት አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓት ላይ መቀመጫቸውን በመዲናዋ ያደረጉ የሦስቱ ዲስትሪክት ዕድለኛ ደንበኞች በተገኙበት የሽልማት ርክክቡ ተካሂዷል፡፡ በሽልማት አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የባንካችን የቦርድ አባላት፣ የበላይ አመራር፣ የሚድያ ተቋማት እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡ በተጨማሪም፤ መቀመጫቸውን ከአዲስ አበባ ውጭ ያደረጉ የባንካችን ዲስትሪክቶችም ጥሪ የተደረገላቸው ዕንግዶች በተገኙበት ለተሸላሚ ዕድለኞቻቸው ሽልማታቸውን አስረክበዋል፡፡
ሽልማቱ በመላው ሀገራችን ለሚገኙ ልዩ ልዩ ደንበኞች መድረሱ፤ የሁሉም ምርጫ የሚለው የባንካችን መሪ ቃል (Tag line) በዕውን የታየበት ነበር፡፡

በቅርቡ በሌላ ዙር ሽልማቶች እንገናኛለን፡፡

የሽልማት ሥነ ሥርዓቱን ጥቂቱን በፎቶ¬¬ ይመልከቱ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button