ባንካችን አቢሲንያ የብር ሁለት መቶ ሺህ ዋጋ ያላቸውን የምግብ ሸቀጦች ለሙዳይ የበጎ አድራጎት ድርጅት ለገሰ

ባንካችን አቢሲንያ የብር ሁለት መቶ ሺህ ዋጋ ያላቸውን የምግብ ሸቀጦች ለሙዳይ የበጎ አድራጎት ድርጅት ለገሰ

ባንካችን ባሳለፍነው አንድ ዓመት ውስጥ ከመንግሥትና ከተለያዩ ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ለተጠየቁ የድጋፍ ጥያቄዎች ከብር 62 ሚሊዮን በላይ ወጪ በማድረግ ማኅበራዊ ግዴታውን በሚገባ ተወጥቷል፡፡

በ1992 ዓ.ም. ኮተቤ አካባቢ በአጸደ ሕፃናት ትምህርት ቤት ጥቂት ሕፃናትን በማስተማር የበጎ አድራጎት ሥራን አንድ ብሎ ለጀመረው ሙዳይ የበጎ አድራጎት ማኅበር ላለፉት 21 ዓመታት እናቶችን እና ሕጻናትን ማዕከል ባደረገ መልኩ ማኅበሩ የሠራውን ተጨባጭ የበጎ አድራጎት ሥራ ከግምት በማስገባት ባንካችን አቢሲንያ በብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ወጪ የተለያዩ የምግብ ግብዓቶችን በመግዛት የማኅበሩ ቅጽር ግቢ በመገኘት አስረክቧል፡፡

ሙዳይ በጎ አድራጎት ድርጅት በወ/ሮ ሙዳይ ምትኩ የተቋቋመ ሲሆን፣ እናቶችን እና ሕጻናትን ማዕከል ባደረገ መልኩ የሚንቀሳቀስ የበጎ አድራጎት ማኅበር ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ማኅበሩ በኑሮ ደረጃቸው ዝቅተኛ ለሆኑ ከ1100 በላይ ሕጻናት እና እናቶች ምግብ፣ መጠለያ (በማኅበሩ ቅጽር ግቢ ውስጥ እና የቤት ኪራይ በመክፈል)፣ ልብስ፣ የጤና ክትትል እና ለሕጻናቱም የትምህርት ድጋፍ ያደርግላቸዋል፡፡

ባንካችን አቢሲንያ ማኅበራዊ ግዴታን መወጣት የሚለውን አንድ የእሴት መገለጫውን ለወገን ደራሽ በመሆን በተጨባጭ ያሳየበት አጋጣሚ ነበር፡፡ ኑሮ የተጫናቸው እናቶችና ሕጻናት በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተው የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ተከትሎ ማኅበሩን የሚጎበኙ ሰዎች ቁጥር በመቀነሱ እና ባለው ከፍተኛ የኑሮ ውድነት ምክንያት በብዙ ድካም መሰረት ይዟል ከተባለ በጎ አድራጎት ድርጅት በገንዘብ እጦት ምክንያት መበተን ሰለሌለባቸው ባንካችን ይህን ድጋፍ በማድረግ የበኩልን አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ በቀጣይም መሰል ድጋፎችን አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

ባንካችን ባሳለፍነው አንድ ዓመት ውስጥ ከመንግሥትና ከተለያዩ ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ለተጠየቁ የድጋፍ ጥያቄዎች ከብር 62 ሚሊዮን በላይ ወጪ በማድረግ ማኅበራዊ ግዴታውን በሚገባ ተወጥቷል፡፡ ሀገራችን እና ሕዝቦቿ የገጠሟቸውን ችግሮች በተቻለ ለመቅረፍ ባንካችን ያለስስት ለልግስና እጆቹን ዘርግቷል፡፡ በመንግሥት፣ በክልል መንግሥታት እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለቀረቡለት የተለያዩ የድጋፍ ጥያቄዎች፣ በኮቪድ 19 ወረርሺኝ ምክንያት ለተፈጠሩ ማኅበራዊ ችግሮች ባንካችን የበኩሉን ሰፊ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button