የዳያስፖራ ቤት መሥሪያና መግዣ ብድር/Diaspora Mortgage Loan አሠጣጥ ሂደትና መስፈርቶቹ

የዳያስፖራ ቤት መሥሪያና መግዣ ብድር/Diaspora Mortgage Loan  አሠጣጥ ሂደትና መስፈርቶቹ

ቤት መግዛት ወይም የቤት ባለቤት መሆን እጅግ አስደሳች ነገር ነው። ነገር ግን የቤት/የንብረት ግዢን በብድር የመፈጸም ሂደትን እንዲሁም ከብድር ጋር በተያያዘ ከመስፈርቶቹ ጀርባ ያለውን ዓላማ በሚገባ ወይም በበቂ ሁኔታ ላልተረዳ ሰው ግን አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። አንዳንድ ሰዎች እንዲያውም ማሟላት የሚጠበቅባቸውን መስፈርቶች እንዲሁም ተያያዥ የወረቀት ሥራዎች ሲሰሙት ገና በማሰብ ብቻ የተወሳሰበ ሆኖ ይታያቸዋል።

ሆኖም ሒደቱን በሚገባ በመረዳትና በየደረጃው ምን እንደሚጠበቅ አስቀድሞ በማወቅ ትክክለኛ የቤት ግዢ ውሳኔን ብሎም ቤትን ጨምሮ ሌሎች ንብረቶችን የማፍራት ጉዞን ቀላል ማድረግ ይቻላል።

የቤት ግዢን በሚመለከት በተለያየ ሀገራት በሚገኙ ኤምባሲዎች፣ በየኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ እንዲሁም በተለያዩ ሪል እስቴቶች በኩል የሚሰጡ የተለያዩ መረጃዎች ያሉ ሲሆን፣ ለዛሬ በዚህ ጽሑፍ ዳያስፖራ የቤት መሥሪያና መግዣ የብድር አገልግሎት በባንክ በኩል ሂደቱ ምን እንደሚመስልና መሟላት ያለባቸው ብቁ የሚያደርጉ መስፈርቶችን በተወሰነ መልኩ ለመዳሰስ ተሞክሯል።

የብድሩ አሠጣጥ ሂደትና መስፈርቶች፡

የብድር ጥያቄ ማመልከቻ ለባንክ ከመቅረቡ እንዲሁም ሊገዛ የታቀደው ቤት/ንብረት ከመፈለጉና ከመመረጡ አስቀድሞ አመልካቹ የመበደርና የመግዛት አቅሙን ግምት የብድር ባለሙያ ጋር ቀርቦ ማሰላትና ማወቅን የመጀመሪያ ርምጃ አድርጎ ሊወስደው ይገባል። ይህን በማድረግ በዋጋ ግምት ልዩነት ሊፈጠር የሚችል ተጨማሪ ልፋትን መቀነስ ይቻላል።

በቀጣይም ከመበደር አቅም ጋር በተያያዘ ሌላ ውሳኔ የሚፈልገውን የመዋጮ/Equity ቁጠባ መጠንን መወሰንና በውጭ ምንዛሪ በሚከፈት ሂሳብ ውስጥ ማስገባት ወይም መክፈል ይኖርበታል። በዚህም የመኖሪያ ቤት/የንብረት መግዣውን ዋጋ ቢያንስ 20 በመቶ ማዋጣት ይጠበቅበታል።

ዳያስፖራው አገልግሎቱን ለመጠቀም የሚከተሉትን ዝርዝር ሰነዶችና ሁኔታዎች በሂደት ማሟላትም ይኖርበታል፡-

~ተቀባይነት ባላቸው የውጭ ገንዘቦች በአንዱ የሚከፈል መሆኑን፣ ጠቅላላ የደሞዝ መጠን እና የተጣራ ገቢን የሚገልጽ ከቀጣሪው የተሰጠ የቅጥር ደብዳቤ
~ አመልካቹ ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆነ የውጭ ዜጋ ከሆነ የታደሰ ፓስፖርትና የትውልደ ኢትዮጵያዊያን መታወቂያ (ቢጫ ካርድ)
~ የጋብቻ የምስክር ወረቀት ወይም ያላገባ ከሆነ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ
~ከውጭ ሀገር ባንክ የሚላክ ቢያንስ የአንድ ዓመት የሒሳብ መግለጫ
~አመልካቹ ኢትዮጵያዊ ከሆነ የታደሰ ፓስፖርት የመኖሪያ እና/ወይም የስራ ፈቃድ
~ አመልካቹ ሁለት የቅርብ ጊዜ የፓስፖርት መጠን ያለው ፎቶግራፍ
~የአገልግሎቱ ጥያቄ የቀረበው በወኪል አማካኝነት ከሆነ የተወካዩ የታደሰ መታወቂያ ኮፒ ፣ ሁለት የታደሰ ፓስፖርት መጠን ያለው የቅርብ ጊዜ ፎቶ ግራፍ እና የውክልና ማስረጃ
~ የቅጥር ውል ኮፒ
~አመልካቹ በንግድ ሥራ የሚተዳደር ከሆነ ቢያንስ የሦስት ተከታታይ ዓመታት የሒሳብ ዝርዝር መግለጫ
~የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ የምሰክር ወረቀት እና
~የግብር ክፍያ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርበታል
~የሽያጭ ሒደቱን ካጠናቀቀ በኋላ ደንበኛው የሚጠበቅበትን ወርሃዊ ክፍያ በባንኩ ተቀባይነት ባላቸው የውጭ ገንዘቦች (ዶላር፣ ፓውንድ ወይም በዩሮ) መፈጸም አለበት
~የመድን ዋስትና/ብድሩ ከተፈቀደ በኋላ/

ከሥራ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ከላይ የተጠቀሱትን ሰነዶቸ ማሟላት ያልቻሉ አመልካቾች (የቤት ሠራተኞች፣ የልጅ አሳዳጊዎች፣ የአስተናጋጅነት እና የጥበቃ ሥራ ለሚሠሩ) የሚስተናገዱበት መንገድ ያለ ሲሆን፣ በዚህም የመዋጮ ቁጠባው እስክ 50% የሚደርስ እንዲሁም ብድሩ ተከፍሎ የሚያልቅበት ጊዜም 15 ዓመት ይሆናል።

ሆኖም ከላይ የተጠቀሱት ሁኔታዎችና ሠነዶች እንደአሰፈላጊነታቸው ዝርዘሩ ሊያንስ ይችላል፡፡

በመቀጠልም ለግዢ የተመረጠው ቤት ወይም ንብረት ኦሪጅናል ካርታ እና ፕላን ኮፒ ባንክ ዘንድ ቀርቦ በባንኩ በኩል በቀጣይ በሚደረግ ቀጠሮ በባለሙያ (Civil Engineer) ዋጋው እንዲታወቅ ይደረጋል።

የሽያጭ ስምምነቱም ከተፈጸመ በኋላ የሽያጭ ውሉ ከብድር ማመልከቻው ጋር ተሟልቶ መቅረብ ይኖርበታል። ነገር ግን የብድሩ ዓላማ ለግንባታ፣ ለእድሳት እንዲሁም ብድሩ ከወለድ-ነጻ አገልግሎት በኩል የሚስተናገድ ከሆነ የብድር አሠጣጡ በተወሰነ መልኩ ከዚህ የተለየ አካሄድ ወይም ሂደት ይኖረዋል።

በመጨረሻም የሚገዛው ቤት/ንብረት ለብድሩ መያዣ እንዲሆን፣ ከብድርና ከመያዣ ውል ፊርማ በኋላ በሚመለከተው የንብረት ምዝገባ ቢሮ በመያዣነት እንዲመዘገብ ከተደረገ በኋላ ተያያዥ የኢንሹራንስ፣ የቀረጥና የአገልግሎት ክፍያዎች ተፈጽመው ብድሩ ለንብረት ሻጭ አካል (ሪል እስቴት፣ ማሀበር ወይም ግለሰብ ሊሆን ይችላል) እንዲለቀቅ ይደረጋል።

ባነሰ የወለድ መጠን/Interest rate፣ እስከ 80% በሚደርስ ብድር እንዲሁም በ20 ዓመት ጊዜ ውስጥ እንዲከፈል የሚያስችለውንና በብዙ አማራጮች የቀረበውን የባንካችንን ምቹ የዳያስፖራ ሞርጌጅ ብድር አገልግሎትን ይጠቀሙ። በውሳኔዎም ይደሰታሉ! ለተጨማሪ ማብራሪያ ነጻ የደንበኞች አገልግሎት መስመር 8397 ላይ ይደውሉ።

አለማየሁ ስሜነህ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button