በ “መቆጠብ ያሸልማል” እና የ“እንሸልምዎ” ፕሮግራም የዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት ተካሄደ!

በ “መቆጠብ ያሸልማል” እና የ“እንሸልምዎ” ፕሮግራም የዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት ተካሄደ!

አቢሲንያ ባንክ ደንበኞቹን ለማበረታታት የተለያዩ የሽልማት ስጦታዎችን እያዘጋጀ ከዘርፉም የተሻለ ውጤት እያስመዘገበ እንደሆነ ይታወሳል፡፡ ዘንድሮም የውጭ ምንዛሬን ለማሳደግ የተዘጋጀ “የእንሸልምዎ” የሽልማት መርሐ ግብር ለአራተኛ ጊዜ፤ እንዲሁም የተቀማጭ ገንዘብ የማሰባሰብ “መቆጠብ ያሸልማል” መርሐ ግብርን ለሦስተኛ ጊዜ ከታኅሣሥ 23 እስከ ሰኔ 22 ቀን 2014 ዓ.ም አከናውኖ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ተከትሎ የዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት ዛሬ ሐምሌ 14 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ የባንካችን የበላይ አመራሮች፣ የብሔራዊ ሎተሪ ተወካዮችና አመራሮች እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በግራንድ ኤልያና ሆቴል ተካሂዷል፡፡ባንካችን በሁለቱም መርሐ ግብር በድምሩ 189 የሽልማት አይነቶች ያቀረበ ሲሆን በውጭ ምንዛሪ (በእንሸልምዎ) መርሃ ግብር 42 የእጣ አይነቶች እንዲሁም በሀገር ውስጥ ሀብት ማሰባሰብ (መቆጠብ ያሸልማል) መርሃ ግብር ደግሞ 147 የሚሆን የሽልማት አይነቶች አዘጋጅቷል፡፡በመሆኑም በቀጣይ ባንካችን በዕጣ የተለዩ ዕድለኞቹን በተለያዩ የመገናኛ መንገዶች በዝርዝር የሚያሳውቅ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Call Now Button