bankofabyssinia.com

Category: Blog

የዴቢት፣ ክሬዲት እና ቅድመ ክፍያ ካርዶች ልዩነት
Post

የዴቢት፣ ክሬዲት እና ቅድመ ክፍያ ካርዶች ልዩነት

አሁን ላይ በአገራችን ካርዶችን ለግዢ፣ ለወጪ እንዲሁም በተወሰነ መልኩ ለኦንላይን ክፍያ መጠቀም ከግዜ ወደ ግዜ እየጨመረ መምጣቱን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ የካርዶቹም ዓይነት እየጨመረ እንዲሁም የብሔራዊ ባንክ ፈቃድን ተከትሎ ካርዶቹን የመስጠትም ሥራ  ከባንኮች በተጨማሪ በሌሎች አካላት ወይም ድርጅቶች ጭምር እየተከናወነ ይገኛል፡፡ ሆኖም ብዙ ሰዎች በክሬዲት ፣ ዴቢት እና ቅድመ ክፍያ ካርዶች መካከል ያለው መመሳሰልና ልዩነት በግልፅ አይታያቸውም፡፡፡፡...

በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ (Money Laundering)
Post

በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ (Money Laundering)

እንደ የተባበሩት መንግስታት ሪፖርት በዓለማችን  ከ800 ቢሊዮን እስከ 2 ትሪሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ገንዘብ በሕገ ወጥ መንገድ በአንድ ዓመት ውስጥ ይዘዋወራል፡፡ ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያ ሽያጭ፣ ኮንትሮባንድ፣ የተደራጁ ወንጀሎች ተግባራት፣ ዕፅ አዘዋዋሪዎች፣ አሸባሪዎችና ሙሰኛ ፖለቲከኞች የፋይናንስ ወጪያቸውን ለመሸፈን ይጠቀሙበታል። እነዚህ ድርጊቶች ከፍተኛ ትርፍ በሚያስገኙበት ጊዜ፣ ተሳታፊዎች ገንዘቡን የሚቆጣጠሩበት መንገድ መፈለግ አለባቸው። ይኽን የሚያደርጉት ምንጮቹን በመደበቅ፣...

የውጭ ንግድ አገልግሎቶች በምን መልኩ ጥቅም ላይ ይውላሉ?
Post

የውጭ ንግድ አገልግሎቶች በምን መልኩ ጥቅም ላይ ይውላሉ?

ስለዓለም አቀፍ የንግድ ፋይናንስ አሠራርና ሂደትሊታወቁ የሚገባቸው መሠረታዊ ነጥቦች የአገራችን የውጭ ንግድ ተሳትፎና አፈፃፀም ከግዜ ወደ ግዜ እየጨመረ መምጣቱንና ወደ ውጪ የላክናቸው እንዲሁም ወደ ሀገር ውስጥ ያስገባናቸው ምርቶች እና አገልግሎቶች  ጠቅላላ ዋጋ ድምር 27.6 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር እንደ ደረሰ በ2020/21 የታተመው የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ ሪፖርት ያሳያል፡፡ በእዚህ ለኢኮኖሚ ብልፅግና ቁልፍ የሆነ ዓለም አቀፍ የንግድ እንቅስቃሴ...

ማኅበራዊ ኃላፊነት ተፈጥሮአዊ ዕሴታችን፤
Post

ማኅበራዊ ኃላፊነት ተፈጥሮአዊ ዕሴታችን፤

እንደ ሐረግ ለተጠላለፈው ኢትዮጵያዊ ማንነት፤ ክሩም፣ ማጉም አንድ ነው፡፡ በዚህ የአንድነት ማግ የተጠናከረው ኢትዮጵያዊነት፤ ዛሬ ያልተጀመሩ፣ በነገ የማይጠናቀቁ የብዙ ትላንቶች ባለቤት እና በማይሰበር ዐለት ላይ የተዋቀረ “አገር” እንድንሆን አድርጎናል፡፡ በዚህ ዓምድ የተገነባው ባንካችን፣ የቀድሞውን የኢትዮጵያን ስም በመዋስ በታላቋ አገር ታላቅ ተቋም ሆኖ ለመውጣት ከዛሬ 26 ዓመት በፊት “አቢሲንያ” በሚል ስም ተመሠረተ፡፡  መልካም ስም ከመልካም ተግባር...

፲ የፋይናንስ አቅማችንን የምናሳድግባቸው አማራጮች
Post

፲ የፋይናንስ አቅማችንን የምናሳድግባቸው አማራጮች

ለአንድ የንግድ ድርጅት ጠንካራ ሥርዐትና (System) የሰው ኃይል የጀርባ አጥንት  ሊሆን ይችላል። ግን የፋይናንስ ዐቅሙ የተዳከመ ከሆነ ከባድ የሕልውና ሥጋት ውስጥ ይወድቃል። በዚህ የውድድር ዓለም ውስጥ ለመዝለቅ፤ ተመራጭና ተፈላጊ ሆኖ ለመቆየት ግዴታ የገንዘብ ዐቅምን ማሳደግ ይገባል። የፋይናንስ ዐቅማችንን ከምናሳድግባቸው መንገዶች ብዙዎች የሚስማሙባቸውን እነሆ። ፩. የፋይናንስ እቅድ ያዘጋጁ፤ ፋይናንስን ለመቆጣጠርና ግቦችን ለማሳካት የፋይናንስ እቅድ አስፈላጊ ነው።...

የዲጂታል ክፍያ አማራጮች ከጥሬ ገንዘብ ነጻ ለሆነ ማኅበረሰብ
Post

የዲጂታል ክፍያ አማራጮች ከጥሬ ገንዘብ ነጻ ለሆነ ማኅበረሰብ

(DIGITAL PAYMENT OPTIONS for CASHLESSS SOCIETY) ሁሉም የገንዘብ ልውውጦች በባህላዊ መንገድ በሚከናወኑበት ሁኔታ፤ ከጥሬ ገንዘብ ነጻ የሆነ ማኅበረሰብ ማግኘት ያስቸግራል፤ በተለይ ደግሞ ቴክኖሎጂ ባልተስፋፋባቸው አገራት። ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ በዓለም ዙሪያ ያሉ ግብይቶች የዲጂታል ክፍያዎችን በመከተላቸው፤ በጥሬ ገንዘብ መገበያየት ያለፈበት ፋሽን እየሆነ ነው። ከበይነ መረብ ጋር ተያይዞ የተፈጠሩት የዲጂታል ክፍያ ሥርዐቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ ወደ...

የሞባይል ባንኪንግ ደኅንነት ምክሮች
Post

የሞባይል ባንኪንግ ደኅንነት ምክሮች

ትላንት የባንክ አገልግሎት ጊዜ የሚወስድ ነበር። ዛሬ፣ ብዙ አማራጮች አሉን፤ አንደኛው የሞባይል ባንኪንግ ነው፡፡ ታዲያ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያዎች ደኅንነታቸው የተጠበቀ ነው? አዎ! የሞባይል ባንኪንግ ደኅንነቱ የተጠበቀ ብቻ ሳይሆን በጣም ምቹና ፈጣን፤ በየቅርንጫፎች በመሔድ የሚመጣውን መስተጓጎልን የሚያስወግድ፤ በቀላሉ ገንዘብዎን ለመቆጣጠርና ለማስተዳደር የሚመች መንገድ ነው። የሞባይል ባንኪንግ የተለያዩ የባንክ መተግበሪያዎችና ዘዴዎች በመኖራቸው ደኅንነቱ የተጠበቀ ነው። መተግበሪያን በሚጠቀሙበት...

7 መሠረታዊ የብድር መሥፈርቶች እና የባንኮች የብድር አሠጣጥ ሂደት
Post

7 መሠረታዊ የብድር መሥፈርቶች እና የባንኮች የብድር አሠጣጥ ሂደት

የባንኮች የብድር  መመሪያና ፖለሲ ከባንክ ባንክ የተለያየ እንደመሆኑ መጠን፣ የብድር አሰጣጥ ሂደቱም በተወሰነ መልኩ ከተቋም ተቋም የተለያየ ነው፡፡ ነገር ግን ባንኮች የብድር ማመልከቻ ከመቀበል ጀምሮ ደንበኛ ወይም ተበዳሪ የሚፈልገውን የብድር መጠን ለመፍቀድ እንዲሟላ የሚፈልጉት፣ የጋራ መሠረታዊ ቅድመ ሁኔታዎች እንዲሁም መስፈርቶች አሉ፡፡ አነዚህን መስፈርቶችና ጉዳዮች በሚገባ መገንዘብና አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ በሂደት ማሟላት የብድር ጥያቄ ውድቅ እንዳይሆን...

ከስዊፍት (SWIFT)  ጋር ይተዋወቁ
Post

ከስዊፍት (SWIFT) ጋር ይተዋወቁ

የሁለተኛው የዓለም ጦርነት መጠናቀቅን  ተከትሎ የቴክኖሎጂ አብዮት በምድራችን ተቀጣጥሏል ማለት ይቻላል፡፡ በጦርነቱ የተሳተፉ አካላት የደረሰባቸውን ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ሥነ ልቡና ቀውስ ለመጠገን በርካታ ተግባራትን ፈጽመዋል፡፡ ፊታቸውንም ወደ ለውጥ በማዞር በኢኮኖሚ የበለጸጉ አገራትን ለመፍጠር ችለዋል፡፡ በጦርነቱ በአገራት መካከል የተፈጠረውን ርርቆሽ ለማቀራረብ፣ የእርስ በእርስ ትስስርና ግንኙነትን ፈጥረዋል፡፡ ለዚህም እንዲረዳ በኔትዎርኪንግ ቴክኖሎጂ የተለያዩ የመገናኛ አውታሮችን ፈልስፈዋል፡፡  “ዓለም መንደር ሆናለች”...

ሞባይል ባንኪንግ: የዘመኑ ገጸ-በረከት
Post

ሞባይል ባንኪንግ: የዘመኑ ገጸ-በረከት

ዘመን የሚወልዳቸው አዳዲስ ግኝቶች፣ የሰውን ልጅ ውስብስብ ሕይወት በማቅለል ረገድ የሚያበረክቱት አስተዋጽዖ ቀላል የሚባል አይደለም። ከባዱን ሸክም ማቅለል፤ ሩቅን መንገድ ማቅረብ፤ ዳር የሆነውን ወደ መሐል ማምጣት ተችሏል። የዘመን ስጦታዎች ሰፊውን ዓለም በማጥበብ፤ ጠባቡን ሰፈር በማስፋት፤ ከአንዱ ጫፍ ወደ ሌላኛው ጥግ መቅረብ የሚቻልበትን ዕድል ፈጥረዋል። የተፈጠሩት ዐዳዲስ የዘመን ስጦታዎች፣ በየጊዜው እየሠለጠኑ እና እየተሻሻሉ የሚመጡ በመሆናቸው ሁል...

Call Now Button