በአካባቢያችንን የሚገኘው ዕድር ቤት አዳራሽ አናት ላይ የተሰቀለው ድምፅ ማጉያ ከመኖሩ በፊት፣ ጋሽ ፉናና የሚባሉ ጥሩንባ ነፊ ነበሩ፡፡ ጋሽ ፉናና ካልተኙ በስተቀር ጡሩምባዋ ከእጃቸው አትለይም፡፡ እኛም በልጅታችን፣ እንዲያስነፉን እንለምናቸው ነበር፤ እርሳቸውም ልጅ ስለሚወዱ አይጨክኑብንም፡፡ ነገር ግን እንደርሳቸው በጣም ማስጮኽ ስለማንችል ባገኘናቸው ቁጥር እንዲያስደግሙን ደጋግመን እንጠይቃቸዋለን፡፡የጋሽ ፉናና ጥሩንባ በጣም ስለምትጮኽ የሰፈር ሰዎች “የሞተን ይቀሰቅሳል” ይላሉ፡፡ ነገር...
Category: Blog
ሰውን “ሰው” ለማድረግ
ሰውን “ሰው” ያደረገው ምንድን ነው? ክብሩ ነው፣ ዕውቀቱ ነው፣ ሀብቱ ነው፣ ሕልሙ ነው?……. ጥያቄ አይደለም ….…. ግን ጥያቄ ቢሆንስ ……… መልሱ ሁሉም ናቸው ማለታችን አይቀርም፤ ምክንያቱም ሰው “ሰው” የሚሆንበት መንገድ ልዩ ልዩ በመሆኑ፣ ይህ ነው ብሎ መወሰን ስለማይቻል ነው፡፡ የተለያዩ ባህላዊ ልምዶች የበዙባት ኢትዮጵያ፣ እንደ ሕግ ተወስደው የሚተገበሩ በርካታ የኑሮ ዘይቤዎች አሏት፡፡ እነዚህ ዘይቤዎች ሕይወትን...
ተለዋዋጭ በሆነው የኑሮ ሁኔታ ውስጥ ሴቶች ጠንክረው እንዲወጡ!
በየዘመናቱ እየተነሡ በታሪክ መዝገብ ላይ ደምቀው የተጻፉ እንስት ጀግኖች ብዙ አሉን፡፡ አገርን በመገንባት ሒደት ከመሳተፍ እስከ ድንቅ አሻራ እና ቅርሶችን ያሳረፉ፤ በዓለም መድረክ ላይ ኢትዮጵያን ከፍ አድርገው ስሟን ያስከበሩ እልፍ ሴቶች አሉን፡፡ ከክርስቶስ ልደት በፊት 1000 ዓ.ዓ ወደ ኋላ ተጉዘን የምናገኛት ንግሥተ ሳባ፤ ከዛሬ 400 ዓመታት የነበረችው ንግሥት ወለተ ጴጥሮስ፤ ብዙም ሳንርቅ 100 ዓመታትን ተጠግተን...
በበዓላት የሚያጋጥሙ ከፍተኛ የገንዘብ ወጪዎችን እንዴት በቀላሉ መቀነስ ይቻላል?
በኅብረ ብሔራዊ ማንነት የደመቀች ኢትዮጵያ፣ የበርካታ ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶች ባለቤት ናት፡፡ እነዚህ እሴቶችዋ ደግሞ ሀገራዊ ማንነት ከመፍጠር ባሻገር በዓለም ላይ ተለይታ እንድትታወቅ አድርገዋታል፡፡ ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ዕሴቶች ካዋለዳቸው ጉዳዮች መካከል ዋነኛው በዓላት ናቸው፡፡ በዓላት ብሔራዊ ሆነው በዕረፍት ቀናት የሚከበሩ በመሆናቸው ሕዝቦች አምረውና ደምቀው የሚታዩባቸው፤ ከመቼውም ጊዜ በላይ አጊጠውና ተውበው የሚያሳልፉበት ነው፡፡ አሮጌው በዐዲስ የሚቀየርበት፤ የሚበላ፣...
የገና በዓል የመጠያየቅ እና ስጦታ የማበርከት ትውፊት
በሰው ልጆች ላይ የደረሰው የዘመናት ፍዳ፣ ከተስፋ በስተቀር ነገን አሻግረው የሚያዩበት ቀዳዳ ትንሽ ነው፡፡ የብሥራቱን ዜና ለመስማት፣ ወደ አዲስ ዘመን ለመሸጋገር ብዙ ሥቃይ እና ብዙ ፈተናዎችን ማለፍ ግድ ብሏል፡፡ በዚህ የፍዳ ወቅት በየጊዜው የተነሡ ነቢያት፣ ሰዎችን በተስፋ መቁረጥ ውስጥ እንዳይወድቁ ቢያበረቱም፤ ጊዜው የመርገም በመሆኑ አንዳቸውም ለጽድቅ አልበቁም፡፡በኀዘን ውስጥ ደስታን ማሰብ፤ በመውደቅ ውስጥ መነሣትን፤ በጨለማ ዓለም...
7 ለዳያስፖራ ቤት መሥሪያና መግዣ ብድር ብቁ የሚያደርጉ መሠረታዊ ሂደቶችና መስፈርቶች
ቤት መግዛት ወይም የቤት ባለቤት መሆን እጅግ አስደሳች ነገር ነው። ነገር ግን የቤት/የንብረት ግዢን በብድር የመፈጸም ሂደትን እንዲሁም ከብድር ጋር በተያያዘ ከመስፈርቶቹ ጀርባ ያለውን ዓላማ በሚገባ ወይም በበቂ ሁኔታ ላልተረዳ ሰው ግን ትንሽ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። አንዳንድ ሰዎች እንዲያውም ማሟላት የሚጠበቅባቸውን መስፈርቶች እንዲሁም ተያያዥ የወረቀት ሥራዎች ሲሰሙት ገና በማሰብ ብቻ የተወሳሰበ ሆኖ ይታያቸዋል። ሆኖም ሒደቱን...
ከዳያስፖራ ወገኖቻችን ምን ይጠበቃል?!
የሰው ልጆች በምድር ላይ እስከኖሩ ድረስ የተጠናቀቀ ወይም ያለቀ አገር የላቸውም፡፡ አገር ሁል ጊዜ ሥራ የምትፈልግ በመሆኗ በትውልድ ቅብብሎሽ የምትደወር ጥጥ ናት፡፡ ምንም እንኳን በየዘመናቱ ልቃቂት ቢበዛባትም ጥጡን እየፈተለች ትጥላቸዋለች፡፡ ኢትዮጵያ ደግሞ ለዘመናት በልጆችዋ እጆች የተሠራች ያማረች ፈትል ናት፡፡ አገር ከልጆችዋ የምትጠብቃቸው እና የምትፈልጋቸው መሥዋዕቶች በየዘመናቱ ይኖራሉ፡፡ ኢትዮጵያ ዳር ድንበሯ ተጠብቆና ሉዓላዊነቷ ተከብሮ የኖረች በትላንቱ...
፯ የገንዘብ ፍሰትን ለማሻሻል የሚረዱ ስልቶች
ብዙ ጊዜ ውስብስብ የሆኑ ጉዳዮች ንግድ ላይ ያጋጥማሉ። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ከቁጥጥር በላይ በሆኑ፣ በውጫዊ ኹነቶች ምክንያት በንግድ እንቅስቃሴዎች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖዎች ይፈጠራሉ። ግን ልክ እንዲዚህ ዐይነት ችግር ቢገጥምዎትስ? በቤትዎ ሽንቁር ጠብ እያለ የሚገባው ፍሳሽ፣ ከእግርዎ በታች ቀስ በቀስ እየሞላ ውኃው ጭንቅላትዎ ላይ ቢደርስስ? በተለይ ዋና የማይችሉ ከኾነ! ነገሩ አለቀ። ለበርካታ ዓመታት የደከሙበት ንግድ መፍትሔ...
የግል ገቢና ወጪያችንን እንዴት እናመጣጥን?
ብዙዎቻችን በስም ለምናውቀውና በተደጋጋሚ ለምንሰማው ቃል እንግዳ አይደለንም፤ የምናውቀው ስለሚመስለን ደግሞ ለጉዳዩ ያለን ትኩረት ይቀንሳል፡፡ ግን ጉዳዩ ከምንም በላይ የሚያስፈልገንና የሚገባን ሆኖ ስናገኘውስ… ቅርባችን የኾነው ሩቅ ይኾንብናል፡፡ ዛሬ ላይ ቅርባችን የኾነውንና የበለጠ በቅርበት ልናጤነው ስለሚገባን ጉዳይ ልናወጋችሁ ወደድን፡፡ እንደምንተነፍሰው አየር በማይቀር የሕይወት ሕግ ውስጥ ኹላችንም በጉዳዩ ላይ አለንበት፡፡ ለተቀመጠው ለሚሮጠው፤ ለምንደኛውም (ለደሞዝተኛው) ለባለሀብቱም ከዚኽ ሕግ...
ክቡር አርቲስት ለማ ጉያ
ኢትዮጵያ ባሕረ ጥበባት፤ የበርካታ ጠቢባን መፍለቂያ ማዕከል ናት። በየዘመናቱ የሚነሡ፣ ከአብራኳ የወጡ ልጆችዋ፣ ከፍ ካለው ክብሯ እኩል ስማቸውንና ስሟን ከፍ በማድረግ ታሪክ፣ ትውልድና ዘመን የማይሽረው አሻራ አኑረው ያልፋሉ። በጥንታዊቷ ይኹን በዘመናዊቷ የኢትዮጵያ ታሪክ ተከሥተው የራሳቸውን ጡብ ለማኖር ብቅ የሚሉ፣ በዐዳዲስ መንገድ እየመጡ የሚያስደምሙ የአገር ዕንቁዎችን አገራችን አጥታ ዐታውቅም፤ ወደፊትም አታጣም። በሥነ ጽሑፍ፣ በኪነ ሕንፃ፣ በሥነ...